ስፖርት፣ የባህል፣ ቱሪዝም እና የመንግሥት ኮሙኒኬሽን (የመገናኛ ብዙኃን) ዘርፍ

ስፖርት፣ የባህል፣ ቱሪዝም እና የመንግሥት ኮሙኒኬሽን (የመገናኛ ብዙኃን) ዘርፍ

ስፖርት፣ የባህል፣ ቱሪዝም እና የመንግሥት ኮሙኒኬሽን (የመገናኛ ብዙኃን) ዘርፍ

በስፖርት ዘርፍ፦ በቤ/ጉ/ክ/መ/ስፖርት ኮሚሽን በ2018 በጀት ዓመት የተከናወኑዋናዋና  ተግባራት

  1. በታዳጊ ወጣቶች ስልጠና ልማት  የተተኪ ስፖርተኞች ቁጥር ከማሳደግ አንፃር ኮሚሽኑ በርካታ ተጨባጭ ለዉጥሊያመጡ የሚችሉ እና የክልሉ ብሎም የሀገር ተስፋ ሊሆኑየሚችሉ ታዳጊዎችን ማሰልጠን ዋና ተግባሩ በማድረግበርካታ ስራዎችን ሲያከናዉን ቆቷል፡፡
    ዚህም መሰረት በክልሉ በሚገኙ ከተማ አስተዳደሮችናወረዳዎች በ125 የስልጠና ጣቢያዎች 3,750 ታዳጊዎችስልጠናዉን እንዲከታተሉ በማድረግ ሰፋፊ የቴክኒክድጋፎችን በማከናወን ታዳጊ ወጣቶቹ ስልጠናዉንእየተከታተሉ ሲሆን ለስልጠና የሚያስፈልጋቸዉንትጥቅ፣ኳስና ሌሎች የስፖርት ቁሳቁሶችን ከ14 ሚሊዮን ብርበላይ ወጭ በማድረግ እና ግዢዎችን በመፈፀም ለታዳጊወጣቶቹ የማሰራጨት ስራ ተከናዉኗል፡፡
  2. የማዘዉተሪያ ስፍራዎችን በሚመለከት የክቡር አህመድናስር መታሰቢያ ስታዲምን ጨምሮ በከተማ አስተዳደርናበወረዳዎች በቁጥር 52 የተለያዩ ደረጃ ያላቸዉ ኳስሜዳዎችን የማስጠረግ እና የይዞታ ማረጋገጫእንዲሰጣቸዉ በማድረግ በስፓርት ዘርፉ ሰፋፊ አበረታችስራዎች ተከናዉነዋል፡፡
  3. ተወዳዳሪና ብቁ ስፖርተኞችን ከማፍራት አንፃር በፌደራልበተከፈቱ ስፖርት ማሰልጠኛ ማዕከላት (ስፖርት አካዳሚ) ከሌሎች የሀገራችን ታዳጊ ወጣቶች ጋር በመወዳደርበተለያዩ ስፖርት ዓይነቶች 25 የሚሆኑ ታዳጊ ወጣቶችስልጠናቸዉን እንዲከታተል ተደርጓል፡፡
  4. በበጀት ዓመቱ በተለያዩ ስፖርት ዓይነቶች ክልሉን ወክለዉበፌደራል ደረጃ በተወዳደሩ ስፖርተኞች
    • 29 ወርቅ ሜዳሊያ
    • 31 የብር ሜዳሊያ
    • 32 የነሀስ ሜዳሊያ  በአጠቃላይ 93 ሜዳሊያ እና 6 ዋንጫ በማስገኘት በአጠቃላይ 98 ሜዳሊያዎችንና ዋንጫዎችን በማሸነፍ ክልላችንለስፖርቱ እየሰጠ ያለዉን ትኩረት ከፍተኛ መሆኑንማሳያ ነበር ብሎ መዉሰድ ይቻላል፡፡

በባህል፣ ቱሪዝም፣ የክልሉን ብዝሃ-ባህልና ተፈጥሯዊ ሀብቶች ለማስተዋወቅና ለልማት ለማዋል ሰፊ ጥረት ተደርጓል። በክልሉ የሚገኙ የታሪክ፣ የባህልና የተፈጥሮ መስህቦችን (የታላቁ ሕዳሴ ግድብን ጨምሮ) ለሀገር ውስጥና ለውጭ ሀገር ጎብኚዎች ለማስተዋወቅ የቱሪዝም ፕሮሞሽን ሥራዎች ተከናውነዋል። የብሔረሰቦችን ባህል፣ ቋንቋና እሴቶች የሚያጎሉ ሁነቶችና የባህል በዓላት ተዘጋጅተው ተካሂደዋል።

በመንግሥት ኮሙኒኬሽንና የሕዝብ ግንኙነት ዘርፍ፣ የመንግሥትን ፖሊሲዎች፣ ስትራቴጂዎችና የልማት አፈጻጸሞች ለሕዝቡ ክፍትና ግልጽ በሆነ መልኩ የማድረስ ሥራ ተከናውኗል። የሐሰተኛ መረጃዎችንና አ አሳሳች ትረካዎችን በመከላከል፣ ትክክለኛና ወቅታዊ መረጃዎችን ለሕዝብ ለማቅረብ የዲጂታል ሚዲያ አማራጮችና የመገናኛ ብዙኃን አቅም እንዲጎለብት ተደርጓል። ይህም የመንግሥትና የሕዝብ ግንኙነትን የበለጠ በማጠናከር ለልማትና ለሰላም ግንባታው አዎንታዊ አስተዋፅኦ አበርክቷል።

← ወደ መነሻ ተመለስ