የብሎግ ዝርዝር መረጃ

ማኅበራዊ ዘርፍ (ትምህርት፣ ጤና፣ የዜጎች ተፈናቃዮች ማቋቋም እና ወጣቶች/ኮደርስ)

ማኅበራዊ ዘርፍ

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግሥት ባለፉት አምስት ዓመታት የሕዝቡን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል፣ ሰብዓዊ መብቶችን ለማስከበርና የሰብአዊ ሀብት ልማትን ለማረጋገጥ በማኅበራዊ ዘርፍ አበይትና ስትራቴጂካዊ ሥራዎች ተከናውነዋል። የትምህርትና የጤና ተቋማት ተዳራሽነትንና ጥራትን ከማሳደግ ጎን ለጎን፣ በግጭት ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጎችን ሙሉ በሙሉ መልሶ ማቋቋም፣ የሴቶችና ወጣቶች ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተሳትፎን ማረጋገጥ የትኩረት ማዕከል ነበሩ።

በትምህርት ዘርፍ፣ በጸጥታ ችግሮች ምክንያት ተቋርጠውና ተጎድተው የነበሩ በርካታ ትምህርት ቤቶች ፈጣን የጥገናና የመልሶ ማቋቋም ሥራ ተደርጎላቸው ዳግም ወደ ሙሉ አገልግሎት እንዲገቡ ተደርጓል። የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥና ብቁ ተፎካካሪ ትውልድ ለማፍራት የሞዴልና የቦርዲንግ ትምህርት ቤቶች ግንባታና ማስፋፋት የተካሄደ ሲሆን፣ የተማሪዎችን ያቋረጡ ምጣኔ ለመቀነስና የመማር ፍላጎታቸውን ለማሳደግ የትምህርት ቤት ምገባ ፕሮግራም ተተግብሯል። ከዚህ በተጨማሪ የመማሪያ መጻሕፍት አቅርቦትና የዲጂታል ትምህርት መሠረተ ልማቶችን የማስፋፋት ሥራዎች በስፋት ተከናውነዋል።

በጤና ዘርፍ፣ የማኅበረሰቡን መሠረታዊ የጤና አገልግሎት ማግኘት ለማረጋገጥ፣ አዳዲስ የጤና ጣቢያዎችና የሆስፒታል ክፍሎች ግንባታ ከመከናወኑም በላይ የተጎዱ የጤና ተቋማት ተጠግነው ወደ ሥራ እንዲገቡ ተደርጓል። በእናቶችና ሕፃናት ሞት ቅነሳ ላይ ትኩረት በማድረግ የአስቸኳይ ጊዜ ሕክምናና የአምቡላንስ አገልግሎት ተዳራሽነት እንዲያድግ ተደርጓል። በተጨማሪም የመድኃኒትና የሕክምና ቁሳቁሶች አቅርቦት ሥርዓት እንዲሻሻል የተደረገ ሲሆን፣ የወረርሽኝ መከላከልና የማኅበረሰብ አቀፍ ጤና ዘመቻዎች በተቀናጀ መልኩ ተካሂደዋል።

የተፈናቀሉ ዜጎችን መልሶ ማቋቋምን በተመለከተ፣ በክልሉ የመጣውን አስተማማኝ ሰላምና መረጋጋት ተከትሎ በግጭት ምክንያት ተፈናቅለው የነበሩ በርካታ ወገኖች ሙሉ በሙሉ ወደ ቀደመ ቀያቸው እንዲመለሱ ተደርጓል። ተፈናቃዮች ወደ አካባቢያቸው ከተመለሱ በኋላም ጊዜያዊ የሰብዓዊ ድጋፍና የምግብ እርዳታ ከመስጠት ባለፈ፣ መደበኛ ሕይወታቸውን በዘላቂነት እንዲመሩ

በሴቶች፣ ወጣቶችና ዲጂታል ክህሎት ዘርፍ፣ የሴቶችንና የወጣቶችን ኢኮኖሚያዊ ተፌደራላዊ ተሳትፎ ለማሳደግ ሰፊ የሥራ ዕድል ፈጠራና የአነስተኛና ጥቃቅን ኢንተርፕራይዞች የብድርና የመስሪያ ቦታ አቅርቦት ተመቻችቷል። በተለይም በቴክኖሎጂው ዘርፍ ያላቸውን ተወዳዳሪነት ለማሳደግ በተከናወነው አገራዊ ንቅናቄ በ5 ሚሊዮን ኮደርስ ፕሮግራም አማካኝነት 26,714 ወጣቶች በሶፍትዌር ልማት፣ በዳታ አናሊቲክስ እና በዲጂታል ማርኬቲንግ ትምህርታቸውን አጠናቀዋል። ይህ ስኬት ለክልሉ የዲጂታላይዜሽንና የልማት እንቅስቃሴዎች የላቀ የሰው ኃይል አቅም ፈጥሯል።

← ወደ መነሻ ተመለስ