በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግሥት ባለፉት አምስት ዓመታት የራስን የፋይናንስ አቅም በማሳደግ በበጀት ረገድ የነበረውን ጥገኝነት ለመቀነስና ለትላልቅ የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች የሚሆን የፋይናንስ ምንጭ ለመፍጠር አበይት የታክስና የገቢ ሪፎርሞች ተተግብረዋል። የታክስ መረቡን የማስፋት፣ የታክስ ስወራን የመከላከል፣ የግብር ከፋዩን ግንዛቤ የማሳደግና የገቢ አሰባሰብ ሥርዓቱን በዲጂታል ቴክኖሎጂ የመደገፍ ሥራዎች በትኩረት ተከናውነዋል።
በነዚህ ተቋማዊና አሠራራዊ እርምጃዎች ምክንያት የክልሉ የውስጥ ገቢ ስብስብ በየዓመቱ እጥፍ ድብል የሆነ ከፍተኛ ዕድገት አስመዝግቧል። በ2017 በጀት ዓመት 4.6 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 5.06 ቢሊዮን ብር በላይ በመሰብሰብ የእቅዱን 110 በመቶ ማሳካት ተችሎ የነበረ ሲሆን፣ ይህን አፈጻጸም መነሻ በማድረግ በተከናወኑ የገቢ አበልጻጊ አሠራሮች በ2018 በጀት ዓመት የክልሉ የውስጥ ገቢ ስብስብ ከሁለት እጥፍ በላይ በማደግ 10 ቢሊዮን 462 ሚሊዮን ብር በላይ ደርሷል።
ይህ ከፍተኛ የገቢ ዕድገት የክልሉን ጥቅል በጀት ያጎለበተ ሲሆን፣ በክልሉ የሚከናወኑ የትምህርት፣ የጤና፣ የመንገድ፣ የመጠጥ ውሃና የከተሞች ኮሪደር ልማት ፕሮጀክቶች ያለ በጀት እጥረት እንዲከናወኑና እንዲፋጠኑ አስችሏል። ከዚሁ ጎን ለጎን የፋይናንስ ኦዲትና ቁጥጥር ሥርዓቱን በማጠናከር፣ የመንግሥት ሀብት ለታለመለት ዓላማ ብቻ እንዲውል የማድረግና የበጀት አጠቃቀም ውጤታማነትን የማረጋገጥ ሥራዎች ተከናውነዋል።





 ታጣቂዎች የተዘጋጀላቸውን የተሃድሶ ስልጠና አጠናቀው ዛሬ ተመርቀዋል.jpg)
 ታጠቂ ቡድን ጋር የተደረሰው የሰላም ስምምነት.jpg)


 ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግሥት ጋር አብሮ የመስራት የውል ስምምነት.jpg)


