በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግሥት ባለፉት አምስት ዓመታት የሕዝቡን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ፣ የልማት መሠረቱን ለማጠናከርና የኢኮኖሚ ዕድገቱን ለማፋጠን በግብርናው ዘርፍ መሠረታዊና አመርቂ የሆኑ ለውጦች ተመዝግበዋል። ክልሉ ያለውን ሰፊና ለም መሬት፣ የውሃ ሀብትና ተስማሚ አየር ንብረት በአግባቡ ጥቅም ላይ ለማዋል ዘመናዊ የግብርና አሠራሮችንና ቴክኖሎጂዎችን የማስፋፋት ሥራ በስፋት ተከናውኗል።
በሰብል ምርትና ምርታማነት ዘርፍ፣ የተሻሻሉ የምርጥ ዘር ዝርያዎችንና የአፈር ማዳበሪያ አቅርቦትን በማሻሻል፣ የሙያ ድጋፍን በማጠናከርና ሰፊ የሕዝብ ንቅናቄ በመፍጠር በየዓመቱ የታረሰው መሬትና የተገኘው ምርት በከፍተኛ ደረጃ እንዲያድግ ተደርጓል። በዚህም መሠረት በ2017 የምርት ዘመን 1.29 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በዘር ተሸፍኖ 40.2 ሚሊዮን ኩንታል የምርት አሰባሰብ የተመዘገበ ሲሆን፣ በተደረገው የተቀናጀ ጥረት፣ የቴክኖሎጂ አጠቃቀምና የአፈር ማዳበሪያ አቅርቦት ማሻሻያ በ2018 የምርት ዘመን የታረሰው መሬት መጠን ወደ 1.61 ሚሊዮን ሄክታር አድጓል። በዚህም የተገኘው ጥቅል የሰብል ምርት ከ55 ሚሊዮን ኩንታል በላይ በማድረስ ታሪካዊ የምርት ዕድገት ማስመዝገብ ተችሏ
ከሰብል ምርት በተጨማሪ፣ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም፣ በዝናብ ላይ ብቻ የነበረውን ጥገኝነት ለመቀነስና በዓመት ሁለትና ከዚያ በላይ ለማምረት የሚያስችሉ የመስኖ ልማት ሥራዎች ተከናውነዋል። በዚሁ መሠረት በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች 13 የመስኖ ግድቦች ግንባታቸው ተጠናቆ ሙሉ በሙሉ ወደ ሥራ የገቡ ሲሆን፣ ከአነስተኛና መካከለኛ የመስኖ ልማቶች ጋር ተጣጥመው ለአካባቢው አባወራዎች ከፍተኛ የገቢና የምግብ ምንጭ ሆነዋል።
በሌላ በኩል በጠቅላይ ሚኒስትሩ አነሳሽነት የተጀመረውን የ"ሌማት ትሩፋት" መርሃ-ግብር መሠረት በማድረግ የአትክልት፣ ፍራፍሬ፣ የዶሮ፣ የንብ እና የእንስሳት ማምናት ሥራዎች በየቤተሰቡ ደረጃ እንዲስፋፉ ተደርጓል። ከዚሁ ጎን ለጎን የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃን ለማረጋገጥ በተካሄደው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር በቢሊዮናት የሚቆጠሩ ችግኞች የተተከሉ ሲሆን፣ የተበላሹ መሬቶችን የማገገም፣ የአፈር መሸርሸርን የመከላከልና የውሃ አካላትን የመንከባከብ ሥራዎች በባለቤትነት ተከናውነዋል።





 ታጣቂዎች የተዘጋጀላቸውን የተሃድሶ ስልጠና አጠናቀው ዛሬ ተመርቀዋል.jpg)
 ታጠቂ ቡድን ጋር የተደረሰው የሰላም ስምምነት.jpg)


 ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግሥት ጋር አብሮ የመስራት የውል ስምምነት.jpg)


